የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰውሃብት ልማት ኮሚሽኑ በኮሚሽኑ እየተገነባ ያለውን የህፃናት ማቆያ ጉብኝት ተካሄደⵆ

የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰውሃብት ልማት ኮሚሽኑ በኮሚሽኑ እየተገነባ ያለውን የህፃናት ማቆያ ጉብኝት ተካሄደⵆ

ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም

————————————————————————————————

የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን የዞንና የከተማ አስተዳደር የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኃላፊዎች እና የማኔጅመንት አካላት በኮሚሽኑ ተነሣሽነት ለህፃናት ማቆያ እየተገነባ ያለውን የህፃናት ማቆያ ጉብኝት አደረጉ፡፡

የኮሚሽኑ ኮማሽነር ወ/ሮ ባንች ዓምላክ ገ/ማርያም እንደገለፁት ኮሚሽኑ የህፃናት ማቆያ አፈፃፀም መመሪያ ከማዘጋጀት ባለፈ ኮሚሽኑ ሞዴል ሆኖ ለህፃናት ማቆያ የሚሆን ህንፃ ግንባታ አስጀምሮ እየሠራ ያለ ሲሆን ግንባታው በ90 ቀናት እንደሚጠናቀቅ ታሣቢ ተደርጐ እየተሠራ ያለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነሯ አያይዘው የህፃናት ማቆያው በየደረጃው ያለውን የመንግስት ሠራተኞች ልጆቻቸውን ንፁህ በሆነ ማቆያ በማቆየት እና ተረጋግተው ሥራቸውን ለመሥራት እንዲያስላቸው ያለውን ፋይዳ አስረድተው ሁሉም የመንግስት ተቋማት በመመሪያው መሠረት የህፃናት ማቆያ በመገንባት እና ምቹ የሥራ ከባቢ መፍጠር እንዳለባቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

ከየዞኑ የመጡ የሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኃላፊዎችም የክልሉን ተሞክሮ ወስደው በየዞናቸው ተሞክሮውን የሚፈፅበት ሁኔታ መፍጠር እንዳለባቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

All reactions:

3434

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top