በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች መረጃ ማረጋገጥ ስራ የተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄዷል
*******************************,***************************
የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሲቪልሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የመንግስት ሰራተኞች መረጃን የማረጋገጥ ስራ አስመልክቶ ለመምሪያ መንግስት ሰራተኞች የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ አካሂዷል።
የመምሪያው ሃላፊ ወይዘሮ አፀደ ሀይለመለኮት በመድረኩ እንደገለፁት በተወሰኑ ተቋማት መረጃ የማጥራት ስራው መጀመሩን ጠቁመው፣ በቀጣይ በቀሪ ተቋማት ከሰራተኛው ምን ይጠበቃል በሚለው ዙሪያ የተዘጋጀ የግንዛቤ ፈጠራ መድረክ መሆኑን ገልፀዋል።
በሚካሄደው የመረጃ ማጥራት ተግባር ላይ ሁሉም መንግስት ሰራተኛ በግንባር ተገኝቶ መረጃውን ለማረጋገጥ ዝግጁ እንዲሆኑ ሃላፊዋ አስገንዝበዋል።
በመምሪያው የአደረጃጃትና ስራ ምዝና ቡድን መሪ አቶ ንጉስ ሹምየ በአቀረቡት ሰነድ እንዳሉት ደግሞ የመንግስት ሰራተኞች የመረጃ ማጥራት እና ማረጋገጥ በተገቢውና በጥራት ለመፈጸም ያመች ዘንድ የተዘጋጀ አሰራር መሆኑን ተናግረዋል።
የተቋማትና የሲቪልሰርቫንቱ ተግባርና ሃላፊነት እንዲሁም አስፈላጊ መረጃዎችን አስመልከተው አቶ ንጉሱ ሰፊ ማብራሪያና ገለፃ ሰጥተዋል።
ሲቪልሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ባለሞያ ወይዘሮ ገበያ ሀደራ
በበኩላቸው የመንግስት ሰራተኞች የመረጃ ማጥራት ዋና አላማው መረጃን በማዘመን የተሳሳቱ መረጃዎችን ለማጥራት እና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል ያለመ በመሆኑ ሁሉ ሰራተኛ ለተፈፃሚነቱ አጋዥ መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል።
