“ሰላም ለሁሉም ፍጡራን እንደሚያስፈልግ ሁሉ፤ ለሰላም መፈጠር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል” ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)
ባሕር ዳር: ጥቅምት 21/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ በአማራ ክልል ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ያለመ የሰላም ኮንፈረንስ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።
በኮንፍረንሱ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ፣ በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣ የክልል ቢሮ ኀላፊዎች፣ የክልል ተቋማት ዳይሬክተሮች እና ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል።
በአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) ባስተላለፉት መልዕክት የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ እና ቀጣይ የሰላም ሥራዎች ላይ እንደሚያተኩር ገልጸዋል።
ግጭት አውዳሚ፣ ሁለንተናዊ ቀውስን የሚያመጣ፣ ማኅበራዊ እሴቶቻችንን የሚሸረሽር እና የሚያጠፋ ነው ያሉት ዶክተር ዘሪሁን ፍቅሩ “ሰላም ለሁሉም ፍጡራን እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለሰላም መፈጠር ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል” ብለዋል።





All reactions:
2929
