መምሪያው የመንግስት ሰራተኞችን ፋይል ከተለምዶው ወደ ዘመናዊ ፋይል አያያዝ እየቀየረ መሆኑን ገለፀ ፡፡
ደብረ ብርሃን፤ ጥቅምት 15 ቀን /2017 ዓ.ም (ሰሸዞመኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ የመምሪያውን የመንግስት ሰራተኞች ፋይል ከተለምዶው (ማኑዋል) ወደ ዘመናዊ (ድጅታል) ፋይል አያያዝ እየቀየረ መሆኑን ገልጿል ፡፡
የሰሜን ሸዋ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት መምሪያ ኃላፊ ሜሮን አበበ እንደገለፁት፤በሰሜን ሸዋ ዞን መምሪያዎችና ተጠሪ ተቋማት 1ሺ68 የመንግስት ሰራተኞች አሉ፡፡
መምሪያው በወረቀት ተይዞ የነበረውን የመንግስት ሰራተኞች መረጃ ወደ ኮምፒውተር ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ የመቀየር ስራ በጀት መድቦ መጀመሩንና እስከ ህዳር 30 ቀን ድረስ ለማጠናቀቅ መታቀዱንም ገልፀዋል፡፡
ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ስርዓቱ የተፈለገውን የሰራተኞች መረጃ በቀላሉ ለማግኘት፣ እንዳይጠፋና ለሌሎች አደጋዎችም እንዳይጋለጥ ለማድረግ እንደሚያስችልም ጠቁመዋል፡፡
ይህ አሰራር ቀደም ብሎ ከነበረው የመረጃ አያያዝ እንዳይጠፋ የሚያደርገው በክልል ደረጃም ጨምሮ በተለያዩ አማራጮች ማስቀመጥ እንዲቻል ያደርገዋል፡፡
ዘመናዊ አሰራሩ ለዞኑ ብቻ ሳይሆን በወረዳ ደረጃ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችን በተመሳሳይ መልኩ እንደሚቀጥል ኃላፊዋ ገልፀዋል፡፡
መረጃው የዞኑ ኮምኒኬሽን ነው።
