የመንግሥት ሠራተኛው የፌደራል ስርዓቱን በመረዳት ማገልገል እንደሚኖርበት ተገለጸ
**********
/ዜና ፌዴሬሽን/
ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ.ም፣ አዳማ
በተለያየ ደረጃ ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትከተለውን የፌደራል ስርዓትን በመረዳት አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሸነር ክብርት ወ/ሮ ስመኝ ውቤ ገለጹ።
19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን አስመልክቶ በአዳማ ከተማ ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ለመጡ የሲቪል ሰርቪስ አስተዳደሮች እየተሰጠ ባለው የአሠልጣኞች ሥልጠና መድረክ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት ክብርት ወ/ሮ ስመኝ ውቤ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች የሚገኙት የመንግሥት ሠራተኞች ሀገራዊ ለውጥ ያመጣውን መልካም ዕድል በመጠቀም እና ፌደራል ሥርዓትን በመረዳት የአገልጋይነት መንፈስ በመላበስ ሕዝቡን ማገልገል ይኖርባቸዋል ብለዋል።
ምክትል ከሚሸነሯ አያይዘውም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን ላለፉት 18 ዓመታት በተለያዩ ክልሎች አስተነጋጅነት በተለያዩ መርህ ቃሎች እና ዝግጅቶች ሲከበር እንደቆየ ገልጸው ሀገራችን ኢትዮጰያ የበርካታ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቤት መሆኗን በመግለፅ በሕብረብሔራዊ የፌደራል ስርዓት ላይ የሚሰጠው ስልጠና የፌደራል ሥርዓቱን ባለመረዳት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ለመፍታት ገንቢ ሚና እንዳለው እና በዓሉን የታለመለትን ውጤት በሚያስገኝ መልኩ ለማክበር እንደሚያስችል ገልጸዋል።
የስልጠና ዓለማውም በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች ስር ያሉት የመንግሥት ሠራተኞች የፌደራል ሥርዓቱን መረዳት እንዲችሉ እና ብዝሃነትን ባከበረ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል እንደሆነ ምክትል ኮሚሽነሯ ተናግረዋል::
የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ ክቡር አቶ በላይ ወዲሻ በበኩላቸው በሲቪል ሰርቪስ ውስጥ ያለው የሰዉ ኃይል ትልቅ የሀገር ሀብት መሆኑን በመግለፅ ስልጠናውን እስከ ታች ማውረድ ያስፈልጋል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ ኀብረብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት በኢትዮጵያ፣ተግዳሮቶቹ እና የመፍትሄ ሀሳቦቹ በሚል ርዕስ የሕገመንግሥትና ፌዴራሊዝም አስተምህሮ ማእከል ዋና ዳይሬክተር በክቡር ዶ/ር ኃይለየሱስ ታየ እና በኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ በክቡር አቶ በላይ ወዲሻ ፅሑፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/hofethiopian/




All reactions:
2424
